ይህ ገዳም ከዚህ ዓለም ከሚገኘው ምኞት ከሥጋዊ ብዕልና ክብር ተለይቶ እግዚአብሔርን በሥነ ፍጥረቱ እያሰቡ ከወዳጅና ከዘመድ ርቆ በርዕይና በሰሚዕ ከሚነሳው ፍትዎት በመሸሽ በዓት አጽንተው ከዓለም ተገልለው በፆም በጸሎት በቁመት በስግደት በተባሕትዎ እግዚአብሔርን ለማገልገል የወሰኑ ሰዎች የሚባትሉበት ቦታ ነው። መነኩሴ ማለት መናኝ ብቻውን የሚኖር በንጽሕና ሆኖ ገዳማዊ ሕይወትን የሚወድ ሰው ባተሌ ከዓለም ከዘመድ ከሕዝብ ከገንዘብ የተለየ ራሴን (መላ አካሌን) ለእግዚአብሔር ስጥቻለሁ ብሎ/ ቃል ኪዳን የገባ አስኬማ መላእክት የለበሰ ባሕታዊ ማለት ነው (“መጽሐፈ ሰዋሰው ውግስ መዝገበ ቃላት ሐዲስ” በአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ) […] ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ