Entrance to St. John the Baptist & St. Arsema Ethiopian Orthodox Tewohedo Monastery
Entrance to St. John the Baptist & St. Arsema Ethiopian Orthodox Tewohedo Monastery in California
Inside of the Monastery in California
A Peek Inside of St. John the Baptist & St. Arsema Ethiopian Orthodox Tewohedo Monastery in California
Out side activities
Out side activities in the St. John the Baptist & St. Arsema Ethiopian Orthodox Tewohedo Monastery in California
ለትምህርት ፈላጊዎች ማስታወቂያ
የአጭር፤ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ እቅዶች
በእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ፤ በዚህ ታላቅ፤ ሰፊና ታሪካዊ የኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አንድነት ገዳም ቦታ ላይ ለመሥራት ከታሰቡት የአጭር፤ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ እቅዶች መካከል የሚከተሉትን በአስቸኳይ በመሥራት በሰሜን አሜሪካና በሌሎችም ዓለማት ለሚኑሩ ወገኖቻችን የተሟላ መንፈሳዊና ማሕበራዊ አግልግሎትን በመስጠት ለተተኪው ትውልድ የዘለዓለም እርስትና ታሪክ ማቆየት የሚቻል መሆኑን አስቀድመን ማሰብ ከሁላችን ይጠበቃል። በዚህ ታላቅ፤ሰፊና ታሪካዊ የገዳም ቦታ ላይ ዘመን ተሻጋሪ የሆኑ የሚከተሉትን ታላላቅ ሥራዎችን በሚቀጥሉት ዓመታት በመሥራት ሕዝበ ክርስቲያኑ የተሟላ መንፈሳዊና ማሕበራዊ አገልግሎት እንዲያገኝ ማደረግ የኆኅተ ሰማይ ገዳም ዋና አላማ ይሆናል […] ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
Short term, medium- and long-term projects list of the monastery
1-Main Church building and services
● Modern Cathedral Church
● Self restricted and independent praying area
● Standard Cemetery
● Holy water service and Baptismal building to serve members
[…]
Click here to read the full text
የኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ ገዳምን ለመጎብኘት ለሚመጡ እንግዶች የተዘጋጀ መመሪያ
የኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አንድነት ገዳምን በካልፎርንያ ለመጎብኘት፤ ለጸበል፤ ለሱባኤ፤ ለመንፈሳዊና መሕበራዊ አገልግሎት ለሚመጡ እንግዶች የተዘጋጀ መመሪያ/ አስገዳጅ ሕግ … ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
ሥርዓተ ገዳም
ይህ ገዳም ከዚህ ዓለም ከሚገኘው ምኞት ከሥጋዊ ብዕልና ክብር ተለይቶ እግዚአብሔርን በሥነ ፍጥረቱ እያሰቡ ከወዳጅና ከዘመድ ርቆ በርዕይና በሰሚዕ ከሚነሳው ፍትዎት በመሸሽ በዓት አጽንተው ከዓለም ተገልለው በፆም በጸሎት በቁመት በስግደት በተባሕትዎ እግዚአብሔርን ለማገልገል የወሰኑ ሰዎች የሚባትሉበት ቦታ ነው። መነኩሴ ማለት መናኝ ብቻውን የሚኖር በንጽሕና ሆኖ ገዳማዊ ሕይወትን የሚወድ ሰው ባተሌ ከዓለም ከዘመድ ከሕዝብ ከገንዘብ የተለየ ራሴን (መላ አካሌን) ለእግዚአብሔር ስጥቻለሁ ብሎ/ ቃል ኪዳን የገባ አስኬማ መላእክት የለበሰ ባሕታዊ ማለት ነው (“መጽሐፈ ሰዋሰው ውግስ መዝገበ ቃላት ሐዲስ” በአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ) […] ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ